አልሄድም እርቄ
ካንተ ተደብቄ አታየኝም ብዬማ
ግፍ አልሰራም እኔማ ፍቅር ነው አይናማ
አልሄድም እርቄ
ካንተ ተደብቄ አታየኝም ብዬማ
ግፍ አልሰራም እኔማ ፍቅር ነው አይናማ
አታየኝም ብዬማ
ግፍ አልሰራም እኔማ ፍቅር ነው አይናማ
ሽፍንፍን ድብስብስ ያላለ ድብቅብቅ ያላለ
ጽኑ ፍቅር በልባችን ካለ ጥርጣሬም የለ
ሽፍንፍን ድብስብስ ያላለ ድብቅብቅ ያላለ
የፍቅር እምነት በልባችን ካለ ጥርጣሬም የለ
የሚያማልል ኑሮ በአይን ቢታይ
ቃሌ ቃል ነው ከህይወቴ በላይ
ክጄህ ሄጄ አልታይም
የቱ ሰው ነው የትኛው ሀገር
ተቀብሎ ደብቆ የሚያኖር
የፍቅር ነውን
ባንተ ላይ ባንተ ላይ
ሌላ የፍቅር ጸብ ሳታይ
ባንተ ላይ ባንተ ላይ
ሌላ የፍቅር ጸብ ሳታይ
አልሄድም እርቄ
ካንተ ተደብቄ አታየኝም ብዬማ
ግፍ ልሰራም እኔማ ፍቅር ነው አይናማ
አልሄድም እርቄ
ካንተ ተደብቄ አታየኝም ብዬማ
ግፍ ልሰራም እኔማ ፍቅር ነው አይናማ
አታየኝም ብዬማ ግፍ አልሰራም እኔማ
ፍቅር ነው አይናማ
ሽፍንፍን ድብስብስ ያላለ ድብቅብቅ ያላለ
ጽኑ ፍቅር በልባችን ካለ ጥርጣሬም የለ
ሽፍንፍን ድብስብስ ያላለ ድብቅብቅ ያላለ
የፍቅር እምነት በልባችን ካለ ጥርጣሬም የለ
ሽፍንፍን ድብስብስ ያላለ ድብቅብቅ ያላለ
የፍቅር እምነት በልባችን ካለ ጥርጣሬም የለ
በረከት ነው የብርሃን ሙላት
ውስጡም ውጪውም ተችሮታል እውነት
ፍቅር ትልቅ ሀብት
ህይወት ዘርቶ ነፍስን ያለመልማል
ለፍጡራን መድሀኒት ነው ያድናል
ፍቅር እምነት ያጣ
ባንተ ላይ ባንተ ላይ
ሌላ የፍቅር ጸብ ሳታይ
ባንተ ላይ ባንተ ላይ
ሌላ የፍቅር ጸብ ሳታይ
ሌላ የፍቅር ጸብ ሳታይ