በሌለሽበት ቦታ
ብቻዬን ተጉዤ
ሲመሽ እመለሳለሁ
ሃሳብ ትዝታሽን ይዤ
በሌለሽበት ቦታ
ብቻዬን ተጉዤ
ሲመሽ እመለሳለሁ
ሃሳብ ትዝታሽን ይዤ
የቆምሽበት
ቀርቶ ትዝታሽ
ያመላልሰኛል
ባትኖሪ እንኳን በጭራሽ
ዝንት ዓለም ቢያልፍ
እድሜ በተርታ
እኔ ግን እዛው ነኝ
ከተውሽኝ ቦታ
ቢያልፍም ጊዜዉ ቢነጉድ
ሌላ እኔ አለምድ
ይሂድ ጊዜ
ይለፍ እድሜ
አንቺን ስል ቆሜ
ሰማይ ምድር ቢያልፉ
ቃሉ እንደማይጠፋ
በቃልሽ እፀናለሁ
ይህ ነው የኔ ተስፋ
ተራራው ቢሸሽ
ባህርም ወጥቶ ቢፈስ
እኔ ግን ከዛው ነኝ
አይጨንቀኝም የኔስ
ቢያልፍም ጊዜዉ ቢነጉድ
ሌላ እኔ አለምድ
ይሂድ ጊዜ
ይለፍ እድሜ
አንቺን ስል ቆሜ
በሌለሽበት ቦታ
ብቻዬን ተጉዤ
ሲመሽ እመለሳለሁ
ሃሳብ ትዝታሽን ይዤ
በሌለሽበት ቦታ
ብቻዬን ተጉዤ
ሲመሽ እመለሳለሁ
ሃሳብ ትዝታሽን ይዤ
የቆምሽበት
ቀርቶ ትዝታሽ
ያመላልሰኛል
ባትኖሪ እንኳን በጭራሽ
ዝንት ዓለም ቢያልፍ
እድሜ በተርታ
እኔ ግን እዛው ነኝ
ከተውሽኝ ቦታ
ቢያልፍም ጊዜዉ ቢነጉድ
ሌላ እኔ አለምድ
ይሂድ ጊዜ
ይለፍ እድሜ
አንቺን ስል ቆሜ
ሰማይ ምድር ቢያልፉ
ቃሉ እንደማይጠፋ
በቃልሽ እፀናለሁ
ይህ ነው የኔ ተስፋ
ተራራው ቢሸሽ
ባህርም ወጥቶ ቢፈስ
እኔ ግን ከዛው ነኝ
አይጨንቀኝም የኔስ
ቢያልፍም ጊዜዉ ቢነጉድ
ሌላ እኔ አለምድ
ይሂድ ጊዜ
ይለፍ እድሜ
አንቺን ስል ቆሜ