Elige una pista para reproducir
ነ... ነነይ ነነነነ ነነነይ ነነነነ ነነነነይ
ኧረ ደሴ ደሴ ኧረ ቃሉ ቃሉ
እንደዋለ ቀረ ቁምነገሬ ኹሉ
ደሴ ምሳ በልቶ ቦሩም የተኛ
መኪናው ዘለቀ ሞልቶ መንገደኛ
ሞልቶ መንገደኛ (×3)
ማን ወደ ማን ይኾን የሚገሰግሰው (×2)
መቼም ያገናኛል መንገድ ሰው እና ሰው
መንገድ ሰውና ሰው (×3)
በሽተኛው በዛ መድኃኒት አነሰው
ከቶ ምን ፈቀደኝ... ነነነነነነ
አሁን የት ይገኛል ያልተለከፈ ሰው
ያልተለከፈ ሰው (×3)
ኧረ ነይ ዘመዴ እናና ዘመዴ
እናና ዘመዴ እናና ዘመዴ
ለጎን ወዳጅ ቢሹ ዓይን ጥርስን ብለው
ቀን አውጭ መሆን ነው ካላዩ መዝነው
ምን አማረኝ ቢሉ የ'ጅንም በትነው
የ'ጅንም በትነው
ሁለት ያጡ ጊዜ ያም ሞት ነው
ያም ሞት ነው
ኧረ ነይ ዘመዴ እናና ዘመዴ
እናና ዘመዴ እናና ዘመዴ
የገበታሽ ራት አይነትም አልበዛው (×2)
ያው ተስፋሽ ነው እንጂ ፊቴን የሚያወዛው
ፊቴን የሚያወዛው (×2)
ኧረ ነይ ዘመዴ እናና ዘመዴ
ነ... ነነነይ ነነነነ ነነነይ ነነነነ ነነነይ
በሉ እናንተ ሂዱ የ'ኛም ወደዚያው ነው
በሉ እናንተ ሂዱ የ'ኛም ወደዚያው ነው
ወትሮም መንገደኛ ፊት እና ኋላ ነው
ወትሮም መንገደኛ ፊት እና ኋላ ነው
እስላም ክርስቲያኑ ባንድ ውሎ ጾማቸው
እስላም ክርስቲያኑ ገጠመ ጦማቸው
ወደ አምላክ ለመሄድ ቀጠሮ እንዳላቸው
ወደ አምላክ ለመሄድ ቀጠሮ እንዳላቸው
አምላክ ይኼን አይቶ ምነው በረዳቸው
መጪን አዲስ ዓመት ብሩህ ያ'ርግላቸው
የመቻቻል ነበር ጥንትም ትዳራቸው
ቢወራ ቢታማ ቢሰማስ እስከዳር (×2)
ሰው አለ ተብሎ ይፈታል ወይ ትዳር?
ይፈታል ወይ ትዳር (×3)
ኧረ ነይ ዘመዴ እናና ዘመዴ
አንቺ የፍቅር እናት በይ ሌማቱን ስፊ
አንቺ የፍቅር ሀገር ባንድ ሰፌድ ልፊ
ከ'ንግዲህ ነውና በረከትሽ ሰፊ (×2)
ኧረ ነይ ዘመዴ እናና ዘመዴ
እናና ዘመዴ እናና ዘመዴ
ነ... ነነነይ
ኧረ ደሴ ደሴ ገራዶ ገራዶ
አለቀልሽ ልቤ ተንዶ ተንዶ (×2)
ኧረ ነይ ዘመዴ እናና ዘመዴ