Elige una pista para reproducir

Rophnan Drop it again
Representing ya nah mean
ለብሳ ሽፎን ባለወርቅ
ጆሮ ጌጥ አይናም ባለፈርጥ
ክብርተ ነገሯ የሳህለወርቅ
ንግስተ ብላት የለውም ፈርቅ
ላንቺ ይላል ልቤ ስሚማ
የኔ ሰው ብለሽ ስሜን ጥሪማ
ቅኔ ነው ስሜ በይ ዝረፊኝ (ሮፍናን)
ቅድሚያ ግን ቤት ምቺ ግጠሚኝ
ባላገሩን ቃላቱን ገጥመሽ ደግሞ ዜማውን
ዜማውን አውርደሽ ምቺ እስክስታውን
ያንጊዜ አገኘ ውበት መለኪያውን
እኔካ ነው እኔክሽ ነው እኔካ
ነው እኔክሽ ነው እኔካ
ወርደሽ ከኔጋ
በይ እኔክሽ በይ እኔካ
በይ እኔክሽ በይ እኔካ
ስትይ ሰበር ሰካ (አዎ)
በይ እውነት ከሆነ ብቻ
ስትመጪ አይን ይከብሻል (አዎ)
ሁሉም አንቺን ይሉሻል (አዎ)
ሰማው አሜን ታውቂያለሽ (አዎ)
በይ ልቤ መርቆሻል (አሜን)
ከኔ ያድርግሽ አሜን በይ ልመርቅሽ (አሜን)
ልስመርልሽ አሜን በይ ልመርቅሽ (አሜን)
ለብሳለች የክቱን ጥርጥር ቀሚሱን
ታበራለች እንደ ፋኖስ ሞልታለች ቤቱን
ልቤም ይለምዳል አይኔም ይወዳል ቆንጆ ቆንጆውን
በይ ልመርቅሽ የኔ ያድርግሽ አሜን በይ መልሱን
አሜን አሜን ኬር ይሁን አሜን
አሜን አሜን ካንቺው እንድሆን
አሜን በይ ስመርቅሽ
በሩን ክፈች ፍቅሬን ስሰጥሽ
አሜን ብለሽ
መልሰኝ መልሰኝ መልሰኝ
ገባሁ
ልሂድ ጊዮርጊስ ገዳም
ታውቂ እንደ ሞጣ ጊዮርጊስ ጎጃም
እኮ በይ አምባ ጊዮርጊስ ጎንደር
ፒያሳ ነው የኔ ጊዮርጊስ ሸገር
ከዚ ጊዮርጊስ ባሎኒ ጊዮርጊስ
ብዞር ባንቺ ፍቅር ከእንደርታ እስከ አዲስ
ምርቃቴ አልሆነም ረስተሽ አንድ ቃል
ከዚህ ሁሉ ድካም አንድ አሜን ይበቃል
አሜን ያሉት እራት አለ ማልዶ
አሜን ያሉት ጠላት ዋለ ታርቆ
አሜን ያለ ጎበዝ ገባ ማርኮ
አሜን ያልሽው ልቤ መጣ ጋልቦ
ዋሽቶ የማለ ዞረ እግሩ ዛለ
ኬር ያለ ሰው ኳለ ዳረ ወልዶ ሳመ
መራቂው እንትፍ ሲል በኬር ተቀበለ
አዶት ደስ አላት ቤቱ ሞልቶ እያደረ
በለስ በል ይቅናህ በለስ
ካሰብከው ድረስ
ጅረት ሁን ለሰው ትረፍ
እጅህ ይስፋ ሀብትህ ይሁን እስከ ጠረፍ
አትሁን ተረት
ኬር
በኢትዮጵያ ቤት ምርቃት ቃል
እንኳንስ ሰው ዛፍ ያፀድቃል
በይ አሜን በይ ነይ ሰው ሁኚብኝ
አልበዛብሽ አታንሺብኝ
ለብሳለች የክቱን ጥርጥር ቀሚሱን
ታበራለች እንደ ፋኖስ ሞልታለች ቤቱን
ልቤም ይለምዳል አይኔም ይወዳል ቆንጆ ቆንጆውን
በይ ልመርቅሽ የኔ ያድርግሽ አሜን በይ መልሱን
አሜን አሜን ኬር ይሁን አሜን
አሜን አሜን ካንቺው እንድሆን
አሜን በይ ስመርቅሽ
በሩን ክፈች ፍቅሬን ስሰጥሽ
አሜን ብለሽ
ኬር ይሁን በይ አሜን
ልቤን ልስጥሽ ሰው ልሸልምሽ አሜን
ኬር ይሁን በይ አሜን
እንዲሆንልሽ አሜን
ኬር ይሁን በይ አሜን
ፍቅሬን ያዢው የአንቺ ይሁን አሁን
ኬር ይሁን በይ አሜን
ኬር ይሁን በይ አሜን
ልቤን ልስጥሽ ሰው ልሸልምሽ አሜን
ኬር ይሁን በይ አሜን
እንዲሆንልሽ አሜን