የቀረበኝን ሁሉ በፍቅር መዝኜ
የሚሆነኝን ባጣ በልቤ አዝኜ
ትቼው ነበር ሁሉን ነገር
የለም ብዬ ሰዉ በሀገር
የቀረበኝን ሁሉ በፍቅር መዝኜ
የሚሆነኝን ባጣ በልቤ አዝኜ
ትቼው ነበር ሁሉን ነገር
የለም ብዬ ሰዉ በሀገር
ድንገት ሲቀናኝ
ጀግና ማረኩኝ
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
ያ ባተሌዉ የቁርጥ ነዉ
የኔ ነዉ የኔ ነዉ
የስራ ሰዉ ያ ሳተና
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
ለኑሮዉ ሲል ደፋ ቀና
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
ላይ ታች ሲል ቤት ሊያቀና
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
ሲጥር ባየዉ ወደድኩት
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
በወንድነቱ አፈቀርኩት
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
ግራ ጎኑን ብመኘዉ
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
አይኔን ስቦ ማረከዉ
የቀረበኝን ሁሉ በፍቅር መዝኜ
የሚሆነኝን ባጣ በልቤ አዝኜ
ትቼው ነበር ሁሉን ነገር
የለም ብዬ ሰዉ በሀገር
የቀረበኝን ሁሉ በፍቅር መዝኜ
የሚሆነኝን ባጣ በልቤ አዝኜ
ትቼው ነበር ሁሉን ነገር
የለም ብዬ ሰዉ በሀገር
ድንገት ሲቀናኝ
ጀግና ማረኩኝ
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
የባተሌዉ የቁርጥ ነዉ
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
የስራ ሰዉ ያ ሳተና
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
ለፍቶ አዳሪ የወንድ አዉራ
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
እጁን ሰቶኝ ምኑን ልኩራ
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
ላንጥፍለት ወርቀ ዘቦ
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
እግሩን ይጠብ እምባ ዘንቦ
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
ልበል እስኪ ቁጭ ብድግ
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
እግርህ ካለዉ ማዕረግ
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
ያ ባተሌዉ የቁርጥ ነዉ
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
የስራ ሰዉ ያ ሳተና
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
ለኑሮዉ ሲል ደፋ ቀና
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
ላይ ታች ሲል ቤት ሊያቀና
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
ሲጥር ባየዉ ወደድኩት
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
በወንድነቱ አፈቀርኩት
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
ግራ ጎኑን ብመኘዉ
(የኔ ነዉ የኔ ነዉ)
አይኔን ስቦ ማረከዉ