Elige una pista para reproducir
ወደ አንቺ ስመጣ ወደ አንቺ ስመጣ
ወደ አንቺ ስመጣ ነው የኔ አለም አለማ
ወደ አንቺ ስመጣ ወደ አንቺ ስመጣ
ወደ አንቺ ስመጣ ነው የኔ አለም አለማ
ይናፍቃል ሰው ሲሄድ እርቆ
አርጎኝ ተጓዥ ህልሜ አንቺን ደብቆ
በመንገዴ ሳይ በደረስኩበት
ደስታ እና ሀዘን ተፈጥሮ እና ክስተት
ይገርመኛል ተከብቤ በሰው
ጥበብ ስሜን ሰግዳ ብታነግሰው
ብቸኝነት ልቤን እያመሰው
ያንቺ ሀሳብ ሳቄን እያበሰው
ብናገር ከልብ አንድ እውነታ
ስኬቱ ያ ሁሉ ጋጋታ
ያለፍኩት ለኔ የለው ቦታ
አለሜ ወደ አንቺ ስመጣ
ወደ አንቺ ስመጣ ወደ አንቺ ስመጣ
ወደ አንቺ ስመጣ ነው የኔ አለም አለማ
ወደ አንቺ ስመጣ ወደ አንቺ ስመጣ
ወደ አንቺ ስመጣ ነው የኔ አለም አለማ
ህይወት ጉዞ ታሳያለች ብዙ
በሮጡት ልክ እነማ ደረሱ
በሀብታቸው መቼ ጊዜን ያዙ
በስማቸው መቼ ደስታን ገዙ
ሳልረዳት ህይወት እኔም እሷን
ስንከራተት ስፈልግ ትርጉሟን
ተፅፎልኝ አይኖችሽ ላይ አየው
ተገለፀ አንቺን እንዳገኘው
ብናገር ከልብ አንድ እውነታ
ስኬቱ ያ ሁሉ ጋጋታ
ያለፍኩት ለኔ የለው ቦታ
አለሜ ወደ አንቺ ስመጣ
ወደ አንቺ ስመጣ ወደ አንቺ ስመጣ
ወደ አንቺ ስመጣ ነው የኔ አለም አለማ
ወደ አንቺ ስመጣ ወደ አንቺ ስመጣ
ወደ አንቺ ስመጣ ነው የኔ አለም አለማ
ተራራውን የሚያስፈራ ገደል
ችዬ ያለፍኩት አንቺን ሳስብ ነበር
በመንገዴ የከፈልኩት ዋጋ
ያ ጉዞዬ ነበር ወደ አንቺ ጋር
ተራራውን የሚያስፈራ ገደል
ችዬ ያለፍኩት አንቺን ሳስብ ነበር
በመንገዴ የከፈልኩት ዋጋ
ያ ጉዞዬ ነበር ወደ አንቺ ጋር
ወደ አንቺ ስመጣ ወደ አንቺ ስመጣ
ወደ አንቺ ስመጣ ነው የኔ አለም አለማ
ወደ አንቺ ስመጣ ወደ አንቺ ስመጣ
ወደ አንቺ ስመጣ ነው የኔ አለም አለማ