የሰዉ ስጋ እርም ነዉ ብሎ ያለዉ ማነዉ
እኔ እስክበላህ በቃ ማበዴ ነዉ
ሰዉ በልተሻል ብሎ የሚከሰኝ ማነዉ
ብበላህ ብዉጥህ ስሜ ባልጠግብህ ነዉ
ጣቶችህ ገላዬን እየለሰለሱኝ
ከላይ ታች በፍቅር እየደባበሱኝ
መልሰዉ የአንተን ናፍቆት እንዲ የሚያደርገኝ
ለዚህ በሽታዬ መድሀኒት የት ይገኝ
ወይ ወይኔ አንተዬ ናፈከኝ
ይልቀቁን እግሮቻችን ከምድር ከፍ ከፍ
እንበል እንደ አሞራ በፍቅር እንንሳፈፍ
ክንፎች ይብቀሉልን አየሩን እንቅዘፍ
ለፍቅር እስከሆነ አይቆጭም እንለፍ
ና ና ገላ መዉደድ ና ገላ
ና ና ገላ መዉደድ ና ገላ
ዛሬን እንፋቀር የነገን አናዉቅም
ይጣፍጠኛል ፍቅርህ አትሰስተዉ አያልቅም
ና ና ገላ መዉደድ ና ገላ
ና ና ገላ መዉደድ ና ገላ
ከደረትህ መካከል ከእቅፍህ አዉለኝ
ፍቅር ጊዜ አይመርጥም ነጋ መሸ አትበለኝ
እንደ ሰማይ ከዋክብት ፍቅርህን አብዛልኝ
ሁሉን ለኔ አድርገዉ ጊዜህን ግዛልኝ
ናፈከኝ ማለቴ አባይ ነኝ ወይ እኔ
ቀንም ሌት ሳትለይ ሳላጣህ ከጎኔ
በቅርብ እያየሁህ ትናፍቀኛለህ
አሁንም አሁንም ዉል ትለኛለህ
አጠገቤ ሆነህ ጎኔን እያሞከኝ
ሳትሰስት ከፍቅርህ እየመገብከኝ
ምነዉ ሳንለያይ ለአፍታ ሳትቀርኝ
እብደት ነዉ ጤንነት የምትናፍቀኝ
ይልቀቁን እግሮቻችን ከምድር ከፍ ከፍ
እንበል እንደ አሞራ በፍቅር እንንሳፈፍ
ክንፎች ይብቀሉልን አየሩን እንቅዘፍ
ለፍቅር እስከሆነ አይቆጭም እንለፍ
ና ና ገላ መዉደድ ና ገላ
ና ና ገላ መዉደድ ና ገላ
ዛሬን እንፋቀር የነገር አናዉቅም
ይጣፍጠኛል ፍቅርህ አትሰስተዉ አያልቅም
ና ና ገላ መዉደድ ና ገላ
ና ና ገላ መዉደድ ና ገላ
ከደረትህ መካከል ከእቅፍህ አዉለኝ
ፈቅር ጊዜ አይመርጥም ነጋ መሸ አትበለኝ
እንደ ሰማይ ክዋክብት ፍቅርህን አብዛልኝ
ሁሉን ለኔ አድርገዉ ጊዜህን ግዛልኝ
አጠገቤ እያለህ ምን ሆኜ ነዉ የናፈቀኝ
እየዉ ፍቅርህ ሲያሞኘኝ እያየሁህ ናፈቀኝ
አጠገቤ እያለህ ምን ሆኜ ነዉ የናፈቀኝ
እየዉ ፍቅርህ ሲያሞኘኝ