የአንተ መሆን እፈልጋለሁ
ግን እፈራሃለሁ
የልብ እምነትና የሴት ልጅ ክብር
መተኪያ የለዉም አንዴ ቢሰበር
ይቀርብህና ደሞ ይርቃል
ልቤ ይጨነቃል
ድብቅ ነች ትላለህ ልቤን ባታገኝዉ
ልቤን ያገኘህ ዕለት ቅስሜንስ ብትሰብረዉ
ምን አምኜ ልቤን ልስጥህ
መች ተገልጦ ታየና ዉስጥህ
እንዴት ብዬ ልቤን ልስጥህ
መቼ ገባኝ አመጣጥህ
እንዳምንህ አታስገድደኝ
በእርጋታ ፍቅር አለማምደኝ
ዘና አርገህ በጥበብ ያዘዉ
የልቤን እምነቱን ግዛዉ
እንዳምንህ አታስገድደኝ
በእርጋታ ፍቅር አለማምደኝ
ዘና አርገህ በጥበብ ያዘዉ
የልቤን እምነቱን ግዛዉ
የቸኮለ አፍሶ ይለቅማል
መታገስ ይጠቅማል
እጠራራለሁ አላምነዉም ደሞ
ልብህ ከእኔ ጋራ መዝለቁን ለከርሞ
ጊዜ ስጠኝ እስክለምድህ
እስከምወድህ
ልብህም ይወቀዉ ተራ ቁምነገሩን
እኔም እንዳሳይህ የልቤን ሚስጢሩን
ምን አምኜ ልቤን ልስጥህ
መች ተገልጦ ታየና ዉስጥህ
እንዴት ብዬ ልቤን ልስጥህ
መቼ ገባኝ አመጣጥህ
እንዳምንህ አታስገድደኝ
በእርጋታ ፍቅር አለማምደኝ
ዘና አርገህ በጥበብ ያዘዉ
የልቤን እምነቱን ግዛዉ
እንዳምንህ አታስገድደኝ
በእርጋታ ፍቅር አለማምደኝ
ዘና አርገህ በጥበብ ያዘዉ
የልቤን እምነቱን ግዛዉ
እንዳምንህ
እንዳምንህ
እንዳምንህ
እንዳምንህ
እንዳምንህ አታስገድደኝ
በእርጋታ ፍቅር አለማምደኝ
እንዳምንህ
እንዳምንህ
እንዳምንህ
እንዳምንህ
እንዳምንህ አታስገድደኝ
በእርጋታ ፍቅር አለማምደኝ
ዘና አርገህ በጥበብ ያዘዉ
የልቤን እምነቱን ግዛዉ
እንዳምንህ አታስገድደኝ
በእርጋታ ፍቅር አለማምደኝ
ዘና አርገህ በጥበብ ያዘዉ
የልቤን እምነቱን ግዛዉ