ይድረስ ለማስብህ ለማልምህ ለአንተ
ፍቅርህን ለማግኘት ልቤ ከዘመተ
ፍለጋ ከወጣ ቆየ ሰነበተ
ወዴት ነው ያለኸው ጥራው ወደአንተ
አይኔን ስከድን ሁሌ አይሀለሁ
አይኔን ስከፍት ወዲያው አጣሀለሁ
ህልሜ እልም ወይስ አይኔ
ግራ ገባኝ እኔ ወድሃለሁ
አንድ እንሁን እኔ እንደአንተ
ህልምህ ልሁን ያኔ አገኝሀለሁ
እውነት ሆነህ
እስካገኝህ
ና በህልሜ ፍቅር አካፍለኝ
ለአንተ እኮ ነው ቃል ኪዳኔ
ቆሜ እንዳልቀር እዚህ ነኝ በለኝ
ይድረስ ለማስብህ ለማልምህ ለአንተ
ፍቅርህን ለማግኘት ልቤ ከዘመተ
ፍለጋ ከወጣ ቆየ ሰነበተ
ወዴት ነህ ያለኸው ጥራው ወደአንተ
አይኔን ስከድን ሁሌም አይሀለሁ
አይኔን ስከፍት ወዲያው አጣሀለሁ
በእውኔ ነበር ወይስ ህልሜ
ውብ አይኖችህ የሚንከባለሉ
እውነት ነበር ወይስ ቅዠት
የዘላለም ፍቅር ይሁን በሉ
ለአንተ ነበር አለሁልሽ
አይዞሽ በርቺ ብለህ የነገርከኝ
አንተ እኮ ነህ የሚያሞቀኝ
የሚጣፍጥ ተስፋን የመገብከኝ
እውነት ሆነህ እስካገኝህ
ና በህልሜ ፍቅር አካፍለኝ
ለአንተ እኮ ነው ቃል ኪዳኔ
ቆሜ እንዳልቀር እዚህ ነኝ በለኝ