ሆነልኝ
ሞላልኝ
ተሳካ
ልቤ ረካ
መጨረሻውን አይቶ ዕቅዱን አሳክቶ
እፎይ አለ ልቤ በስራው ረክቶ
ወፌ ቆመች ብለው ያቆሙኝ በእግሬ
ይሁኑልኝ ጎኔ በድሌ ቀን ዛሬ
ይሄን ሁሉ ዘመን ስደክም ስለፋ
ስላልቀናኝ ቶሎ አልቆረጥኩም ተስፋ
እንቅፋቱ በዝቶ ስወድቅ ስነሳ
ይኸው እዚህ ደረስኩ ፈተናው ተረሳ
አ ተስፋዬ
ጉልበቴ
ኃይሌ አድርጌ መሠረቴ
ብርታቴን
አ ይኸው
አዎ ሕልሜ
ጊዜ ፈቅዶ ደረሰልኝ
ሞላልኝ
ሆነልኝ
ሞላልኝ
ተሳካ
ልቤ ረካ
መጨረሻውን አይቶ ዕቅዱን አሳክቶ
እፎይ አለ ልቤ በስራው ረክቶ
ወፌ ቆመች ብለው ያቆሙኝ በእግሬ
ይሁኑልኝ ጎኔ በድሌ ቀን ዛሬ
ችለው ከጠበቁት ቀን መምጫውን ያውቃል
ነገ ስለራሱ ሲደርስ ይጨነቃል
የሰው ልጅ ከፀና በመንፈስ ባካሉ
ይሳካል አንድ ቀን የታሰበው ሁሉ
አ ተስፋዬ
ጉልበቴ
ኃይሌ አድርጌ መሠረቴ
ብርታቴን
አ ይኸው
አዎ ሕልሜ
ጊዜ ፈቅዶ ደረሰልኝ
ሞላልኝ
መጨረሻውን አይቶ ዕቅዱን አሳክቶ
እፎይ አለ ልቤ በስራው ረክቶ
ወፌ ቆመች ብለው ያቆሙኝ በእግሬ
ይሁኑልኝ ጎኔ በድሌ ቀን ዛሬ
መጨረሻውን አይቶ ዕቅዱን አሳክቶ
እፎይ አለ ልቤ በስራው ረክቶ
ወፌ ቆመች ብለው ያቆሙኝ በእግሬ
ይሁኑልኝ ጎኔ በድሌ ቀን ዛሬ