Elige una pista para reproducir
መሸ ደህና እደሩ ናፍቆት ነው ልማዴ
መቼም መተው መርሳት አያውቅበት ሆዴ
ለታቦት ይሳላል የተጨነቀ ሰው
ማን አለኝ እንዳንቺ ነፍሴን የወረሰው
ኮከብ ተገለጠ አዬ ተሸኘ ፀሀይ
ልቤ ረጋ ሳይል አይኔ ሰው ሳያይ
እሷም አልተገኘች ብደክም ብለፋ
ፍቅሬስ አቦል ነበር አጣጪው ባይጠፋ
መሸ ደህና እደሩ ናፍቆት ነው ልማዴ
መቼም መተው መርሳት አያውቅበት ሆዴ
ለታቦት ይሳላል የተጨነቀ ሰው
ማን አለኝ እንዳንቺ ነፍሴን የወረሰው
የመውደዴን ሚስጥር አዬ እንዴት ልሸፍነው
ማናገር ይወዳል መለየት ክፉ ነው
አንቺማ የሆድሽን አዬ መቼ ተነፈሽው
ዝም ብለሽ አይደል ወይ ጥለሺኝ የሄድሽው
መሸ ደህና እደሩ ናፍቆት ነው ልማዴ
መቼም መተው መርሳት አያውቅበት ሆዴ
ለታቦት ይሳላል የተጨነቀ ሰው
ማን አለኝ እንዳንቺ ነፍሴን የወረሰው
ብርዱ እየበረታ አዬ በግንቦት በሰኔ
ምነው በክረምቱ ትርቂያለሽ ካይኔ
እስኪ ልሂድ ገዳም አዬ ልግባ ልመልንኩሰው
አንቺስ እርምም የለሽ ትደርሻለሽ ከሰው
ትደርሻለሽ ከሰው ትደርሻለሽ ከሰው