Elige una pista para reproducir
አዎ ቅጅልኝ ፍቅር የሚሰብር
አዎ ለምን አንደምጠጣ ታውቂያለሽ) ሰው የሚቀይር
ፍቅር ተስፋ ቢስ አረግሽኝ
ልንገርሽ በጨለማ ትተሸኝ
ፍቅር ትልቅ ዉሸት መውደድ ቃል ለሚቀደድ
ይኸው በሷ ክህደት ነፍሴን ነፍሴን እዯት ሁሌ በእሳት ስትነድ
አዎ ፍቅር በወጣትነት ደስታ ነው የሚመስለው እስትከዱበት
ኑሩ በጊዚያቹ በሉ ሁሉን እዩበት
ስጡ ልባችሁን እስክትቀጡበት
አዎ ፍቅር ለካ የልብ ስር
ሰው የሚያየው ከባድ ሀዘን ሲኖር በዚች ምድር
ስንጀምረው ትዝ ይለኛል ነው በተስፋ
እንዲ ሊሰባበር ቃልሽ ሲጀምር ሊጠፋ
ክፉ አንቺ አደለሽ እድሌ ነው ያጠፋው
ካንቺ ጋር በደም ክር ሁሌ ይህ ልቤን የሰፋው
ትዝ ይለኛል ያ የደስታ ጊዜ ነህ የልቤ ጌታ
ያልሽው ቃል ኧረ የት ገባ
ያልሽው ቃል የሰጠሸኝ ቃል ኧረ የት ገባ
የሷ ነው ስጦታ ይሄ ትዝታ
የሷ ነው ስጦታ ይሄ ትዝታ
ቆይ እንዳትዘጊው ስልኩን
ቢያንስ የኖርነውን ፍቅር አስታውሺ ትላንቱን
ላንቺ የሩቁን እኔ አምኖረውን አሁን
ትዝታሽ የነገን መግቢያ ዘግቶብኛል በሩን
ሄሎ አትሰማኝም ዘግታዋለች ልቧን አታየኝም
ጨክናለች በኔ አትወደኝም እረሳችኝ ክዳ አሁን አታቀኝም
ሀሰት መልሱ ፍቅርን እንደዛ ብቻ ማን ነው ያረገው
ተረቱ ላይ አሉ ፍቅር መባረክ ነው ውሸት ውሸት
ሁሉም አለው ሰባራ ልብ እሱ ነው እውነት
ቆይ እንዳትሉ የሚሆነው ሁሉም ለበጎ ነው
የውሸት ሳቅ የደበቀው ሀዘን ሁሉም ጋር ነው ያለው
ይገባሻል እያንዳንድሽ ያቀዋል የሚያቀው
ለዛ ለው ምትስቀው አይኖችህ እምባ አዝለው
አልረሳሁትም ትዝ ይለኛል ልክ እንደ ህልም
ያ የደስታ ጊዜ የማይገኝ የትም
ያሰረኝ ያ ፍቅርሽ አይለቀኝም
ያ ክፉ ትዝታሽ አይለቀኝም
የሷ ነው ስጦታ ይሄ ትዝታ
የሷ ነው ስጦታ ይሄ ትዝታ
ይገርመኛል ሰውነት ይሄ ዘመን አሁን ያለንበት
የሰረቀው የሚከበር የሚከዳው የሚፈቀርበት
እሚፈቀረው የሚከዳ የተጎዳው ነው ባለ እዳ
የተጎዳው ነው ባለ እዳ
ያስቀኛል ድካማችን ለማስመሰል እሩጫችን
ቆይ ለየትኛው ስማችን መጨካከን መጋደሉ
እንቅልፍ አቶ መቀመሩ ቆይ ለየትኛው ጊዜያችን
ከፈልኩኝ ከፈልኩኝ መስዕዋትነት
ላንቺ መኖር ላንቺ መኖር ሆኖ እብደት
ለእውነት ለፍቅር ስንከራተት በጨለማ ብቸኝነት
ጠፍቷል የኔ መንገድ አዎ ፍቅርሽ ልቤ ሲነዳው
ቀረው ይሄ ትዝታሽ አዎ ሆኜ መንገደኛሽ አዎ
የሷ ነው ስጦታ ይሄ ትዝታ
የሷ ነው ስጦታ ይሄ ትዝታ
አዎ ፍቅር የሚሰብር አዎ ሰው የሚቀይር
ተስፋ ቢስ አረግሽኝ በጨለማ ትተሸኝ