Elige una pista para reproducir
ኢትዮጵያውያኖች እንደምን አላችሁ
ኢትዮጵያውያኖች እንደምን አላችሁ
የአንዲት እናት ልጆች ባእድ የሌለባችሁ
ተው ተው ተው
እሯ እላለሁ
እሯ በልዬ
የዚያ ጀግና ልጅ
የዚያ ሰውዬ
እሯ በል አንተ
እሯ በልዬ
የዚያ ጀግና ልጅ
ግባልኝ
ይህ ይድረስ ለዚያ ሰው
ወራሪውን ለመለሰው
የነፃነት ተምሳሌት አድርጎ
ስሜን ክብር ላለበሰው
ያረክልኝ ብዙ ነው
ከፍዬም የማልጨርሰው
ያረክልኝ ሁሌ አዲስ
በሄድኩበት የምለብሰው
ብጠራው ስምህን
ጀግናውን ስራህን አመት መቼ ይበቃል
በአለም ያለ ጥቁር
ከትውልድ ትውለድ አንተን ያመሰግናል
እሯ ልበላ እንደአንተ ምንም እንኳን ካንተ ባያምርብኝ
እሯ ልበላ እንደአንተ ምንም እንኳን ካንተ ባያምርብኝ
ዛሬ ላይ ምፅፈው የኔ የሚሆን ታሪክ ጨለማ ቢመስልብኝ
ተስፋ አለመቁረጥን ከአንተ ተምሬያለሁ አደራህም አለብኝ
እሯ ልበላ እንደአንተ ምንም እንኳን ካንተ ባያምርብኝ
እሯ ልበላ እንደአንተ ምንም እንኳን ካንተ ባያምርብኝ
ሠከላ አባይን ወለደች
እናቴም እኔን
ቅድሚያ ሰው ደግመው ግን ማነህ ሲሉኝ
ኢትዮጵያ ነው ስሜ
አልወድቅም ለመድረስ እጄ ቢያጥርም
ከበላይ ባልዘልቅም
ባይመስልም አንዴ እንኳ አያቅተኝም
እንደ ቴዎድሮስ ባልደግም
እሯ እላለሁ
እሯ በልዬ
የዚያ ጀግና ልጅ
የዚያ ሰውዬ
እሯ በል አንተ
እሯ በልልኝ
የዚያ ጀግና ልጅ
ግባልኝ ና!
ሠከላ አባይን ወለደች
አሀሀይ ጉማ
አሀሀይ ጉማ
አሀሀይ ጉማ
አሀሀይ ጉማ
አሀሀይ ጉማ
አሀሀይ ጉማ
አሀሀይ ጉማ
ጦቢያው ለይቅርታ ቅደም
ቀድመህ እንዳትተው ድገም
ደግሞ ቢያስቀይምህ ሰልስ
የአባትክን አደራ መልስ
ያኔ በላይ ይዘልቃል
ያንጊዜም ቴወድሮስ ይደግማል
ያንጊዜም አሉላ ራስ ነው
ምኒሊክ ዛሬም ንጉሥ ነው
በልልኝ አንተሰው በልልኝ አንተው ራስህ ላይ
ይቅርበል አንተ ሰው እሯ በልበት ጥላቻ ላይ
አድዋ ዘማች የልጅ ልጅ እኔና አንተ አይደለን ወይ
ሮፍናን ዘምነገደ ጦቢያው የአንተም እንዲያ አይደለም ወይ!
ሠከላ አባይን ወለደች
እናቴም እኔን
ቅድሚያ ሰው ደግመው ግን ማነህ ሲሉኝ
ኢትዮጵያ ነው ስሜ
ከቶ አልቀርም ለመድረስ እግሬ ቢያጥርም
አብዲሳን ባልቀድምም
ሳይጨልም ሳይመሽ ለይቅርታ ላዝግም
ጣይቱን አልሰጥም
እሯ እላለሁ
የልብ አድርስ
የዚያ ጀግና ልጅ
የዩሐንስ
እሯ በል አንተ
እሯ በልልኝ
የጃጋማ ልጅ
ግባልኝ ና!
ሠከላ አባይን ወለደች
ሠከላ አባይን ወለደች
እናቴም እኔን
ሠከላ አባይን ወለደች
እናቴም እኔን
ሁሉም ትውልድ አድዋ አለው
የኔም አድዋ ልቤ ላይ ነው
ቢገፉኝ ፍቅር ማሳየት
በይቅር ልቆ መገኘት
ያንጊዜ አብዲሳ ይደርሳል
በልቤም ባልቻ ይነፍሳል
ዩሐንስ ደሙ ወርቅ ነው
ላልከዳው ጴጥሮስ መልስ ነው
ጠበቁኝ በደም ርሰው
የጥፋት ጉድጓድን ምሰው
በሰባራቸው አፍዘው
ሰባራ ሰንደቅን ይዘው
እንግዲህማ እኔ ልሻል
መርዙን በይቅርታ ልሻር
ከአባቶቼም ባይሆንልኝ
ከአያቶቼ አንድነት ልማር
እሯ ልበል የዛሬ ሰው
ፍቅር ፈሶብኝ ልፈሰው
ልንተባተብ ጀግንነቱን
ከልቤ ላግኝ ምህረቱን
ሠከላ አባይን ወለደች
እናቴም እኔን
ሠከላ አባይን ወለደች
እናቴም እኔን
ጎሽ!
ሠከላ አባይን ወለደች
እናቴም እኔን
አሹ!
ሠከላ አባይን ወለደች
እናቴም እኔን