
አምባሰል
አምባሰል ነው ቤቴ
ነብሴ ለሰለሰች በድምፆችሽ ቃና
ክራር ሲደረደር ሲመታ በገና
ከሠማያት ሠማይ መንጥቃ ወስዳኝ
ጉድፌን አጠራች ልቦናን ሰታኝ
ፍቅር እንዳይጠፋን መንገዱን ስተን
ከፊት እየመራህ አንተው አሳየን
ሠው የፊቱን ትቶን ከኋላ እየቀረ
መያያዝ አቅቶት ስንቴ ተቸገረ
አምባሰል ነው ቤቴ
አክሱም ላሊበላን ጎንደርና ሀረር
ኦሮሞ ደቡብም ሱማሌና አፋር
ከጫፋ አንስቶን የተገማመደው
ማንስ ያሰረውን ማንስ ነው ሚፈታው
የበራችው ፀሀይ ሽታዋ እንዳይጠፋ
ፀድቃልኝ እንዳያት ያቺ የኔን ተስፋ
አስረክሻት ነብሴን ኩነኔ እንዳልገባ
ሰው አድርገኝ ዛሬ ለሠው ልትረፍ የኔ አባ
ኤይኤ
ቀን መ'ቶ ቀን ሄደ
ሠው ቆሟል መቼ ተራመደ
ሚያፈርሰው ሚያቀና
ዘንድሮ በምን ይለይና
ሰማ ወይ ፀሎትሽ
መች ይሆን ናፈቀኝ ሰላምሽ
አምባሰል ነው ቤቴ