Выберите трек для воспроизведения
ሞላ አልሞላ እምልው እህህህ ጉዳይ ቢኖረኝም
አለማመስገን እኔ ከቶ አይሆንልኝም
እኔ እንደልማዴ እህህህ መዘመር ስጀምር
ባስጨነቀኝ ላይ ዛሬም ይገለጣል ክብር
ጉዳይ አለኝ የማዋይህ
ለልቤ ንጉስ ማንጎራጉርልህ
ነገር አለኝ የማዋይህ
ለልቤ ንጉስ ማንጎራጉርልህ
ምስጋናን ልሰዋ ማዳንህን እንዳይ
በእርግጥ ለሚወዱህ መላ አለህ ከሰማይ
ምስጋናን ልሰዋ ማዳንህን እንዳይ
በእርግጥ ለሚወዱህ መላ አለህ ከሰማይ
°°°
ደግሞ እድሉ ደርሶኝ
ደግሞ ሳይገባኝ
ደግሞ በራሱ ፀጋ
ደግሞ ዘምር ካለኝ
ደግሞ እንዲህ እንዲያ የሚል
ደግሞ ቆስቋሽ ለምኔ
ደግሞ የተሰራልኝ
ደግሞ በቂ ነው ለኔ
ያለው አይቀርም አምናለሁ ዝማሬ ከአፌ አይታጣ
የካሳ ጊዜ ይሆናል ቀን ቆጥሮ ለኔ ሲመጣ
እግዚአብሔር ነው ጉልበቴ መዝሙር በሌሊት የሰጠኝ
ቃል ገብቶልኛል አውቃለሁ ላይጥለኝ ደግሞ ላይተወኝ
ያለው አይቀርም አምናለሁ ዝማሬ ከአፌ አይታጣ
የካሳ ጊዜ ይሆናል ቀን ቆጥሮ ለኔ ሲመጣ
እግዚአብሔር ነው ጉልበቴ መዝሙር በሌሊት የሰጠኝ
ቃል ገብቶልኛል አውቃለሁ ላይጥለኝ ደግሞ ላይተወኝ
ያለው አይቀርም አምናለሁ ዝማሬ ከአፌ አይታጣ
የካሳ ጊዜ ይሆናል ቀን ቆጥሮ ለኔ ሲመጣ
እግዚአብሔር ነው ጉልበቴ መዝሙር በሌሊት የሰጠኝ
ቃል ገብቶልኛል አውቃለሁ ላይጥለኝ ደግሞ ላይተወኝ