ላፋቸው ቅርብ ነው አይጠፋም ስሜ
ያልኳቸው አይሹም ዉጣ ዉረዴን
አንገቴን ብደፋ ልብም ከፋ
አለሁኝ አቤት ባይ ሰውም ጠፋ
ያ ሁሉ ጎበዝ ባይ አሁን የት ገባ
ጠቀምኩኝ አገዝኩኝ እኔማ ብዬ
ከስንቶቹ ስከራከር ለስንቱ ቆሜ
አላዋቂን ማሞጋገስ ትርፉ ይሄው ነው
ያናንቃል ጥሩ ሥራ ምስጋና የለው
ለሰው መሳይ ሾካኮቹ ከንግዲ የምለው
ደግ አረኩ!
ተሰማቹ መሰለኝ
ደግ አረኩ!
ያሰብኩትን ተናግሬ
ደግ አረኩ!
ማይሆነኝን ቆራርጬ
ደግ አረኩ!