Выберите трек для воспроизведения
ያስፈራራ ነበር ጨለማዉ
እግዞ እግዞ ሚያሰኘ ነው
ሁኔታ ሲመጣ እየገፋ
ለጥቂት ቀን ቢሆን እምነት ጠፋ
ወየሁ ጠፋሁኝ ብዬ ያለቀልኝ ሲመስለኝ
በድቅድቊ ሌሊት ላይ ጎኔ ቆሞ አበረታኝ
ሁን ሲል የሚሆንለት ቃል አዉጥቶ ሂድ ያለዉ
የማያልፍ የመሰለኝ ያም አለፈ እንዳለፈዉ
ያም አለፈ እንዳለፈዉ
ያም አለፈ እንዳለፈዉ
ያም አለፈ እንዳለፈዉ
ያም አለፈ እንዳለፈዉ
ሆ ብሎ ወጥቶ ነበር ጦሩን አሰባስቦ
አይዞህ የሚል ባይኖር መልካም ቀን አስቦ
እንደሰዉ አይደለም ብለን ያዜምንለት
እደገና አቆመኝ በብዙ በረከት
ሆ ብሎ ወጥቶ ነበር ጦሩን አሰባስቦ
አይዞህ የሚል ባይኖር መልካም ቀን አስቦ
እንደሰዉ አይደለም ብለን ያዜምንለት
እደገና አቆመኝ በብዙ በረከት
ምን አይነት ነገር ነዉ የወረደዉ
ብዙሀኑን ሰዉ እንዲህ ያራደዉ
የሚያተርፍ አይመስልም አመጣጡ
ብዙህ ሐያላኑ እጅ ሰጡ
እኔም ያዉ ሰዉነኝና ያለቀልኝ ሲመስለኝ
በድቅድቁ ሌሊት ላይ ጎኔ ቆሞ አበረታኝ
ሁን ሲል የሚሆንለት ቃል አዉጥቶ ሂድ ያለዉ
የማያልፍ የመሰለኝ ያም አለፈ እንዳለፈዉ
ያም አለፈ እንዳለፈዉ
ያም አለፈ እንዳለፈዉ
ያም አለፈ እንዳለፈዉ
ያም አለፈ እንዳለፈዉ
ያም አለፈ እንዳለፈዉ