Оберіть трек для відтворення
መብከንከንህ ሆና አካልህ
በሃሳብ ቀንተህ ሳያይ ዓይንህ
ስንቱን ጠርጥረህ እራስህ በራስህ
ምን ታይቶህ ነው ማሠሥኅ
የሰው ካላንኳኳህ አይንኳኳም በርህ
ታመን አንተ ብቻ የብቻህ ነች ፍቅርህ
አንተ አትቅበጥ እንጂ አትይ የሰው ጓዳ
አንዳትመስልህ ፍቅርህ አንተን የምትከዳ
ዋስ ነው የራስ ታማኝነት ማንነት
ፍቅርስ ላንተው ነው የሰራት
ቃልህን አክብር እንጂ የኪዳንን ስልጣን
አልፎ አንተን አይነካም ምን ቢጎብዝ ሰይጣን
መቼም የትም ቢሆን ማን ቢሆን ጠንካራ
ጫፍህ የሚደርስ የለም አንተን የሚያስፈራ
መብከንከንህ ሆና አካልህ
በሃሳብ ቀንተህ ሳያይ ዓይንህ
ስንቱን ጠርጥረህ እራስህ በራስህ
ምን ታይቶህ ነው ማሠሥኅ
ቃልህን አክብር እንጂ የኪዳንን ስልጣን
አልፎ አንተን አይነካም ምን ቢጎብዝ ሰይጣን
መቼም የትም ቢሆን ማን ቢሆን ጠንካራ
ጫፍህ የሚደርስ የለም አንተን የሚያስፈራ
ዋስ ነው የራስ ታማኝነት ማንነት
ፍቅርስ ላንተው ነው የሰራት
ከራስህ ከፈራህ መርዙን የቅናትን
አንተም ለሰው ፍራ አትይ የሰው ቤትን
ደስ እንዲልህ ፈልግ ሰው የማታስቀና
ፍርድ ይሄ ብቻ ነው ሕግ አንድ ነውና
ነገርን ነገር ያንሳ አመልን አመል ይርሳ
ምን ይቀብጣት ለባብሳ ታሸታለች አበሳ
ነገርን ነገር ያንሳ አመልን አመል ይርሳ
ምን ይቀብጣት ለባብሳ ታሸታለች አበሳ
የሰው ካላንኳኳህ አይንኳኳም በርህ
ታመን አንተ ብቻ የብቻህ ነች ፍቅርህ
አንተ አትቅበጥ እንጂ አትይ የሰው ጓዳ
አንዳትመስልህ ፍቅርህ አንተን የምትከዳ
ሰው የሌላን ካየ ጥፋት ነው ጠርጥር
የሱም ትታያለች በከፈተው አጥር
ሌላ ቤት ሲቋምጥ ጓዳዋን ለነገር
የሱም ትታያለች በከፈተው አጥር