ቋጥኝ ለመናድ ስጥር
ያደናቀፈኝ ጠጠር
ያሰብሁት ሩቅ ለመጓዝ
የቀጨኝ የቁጠርሁት ጓዝ
ያለምሁት ሰማይ መንካት
የስቀረኝ መስዋዕት መፍራት
ሰማይ ጠፈርን ለመንካት
መክፈል ግድ ነው መስዋዕት
ሁሌ እላለሁ
ሁሌ እላለሁ አይዞኝ
ገና ብዙ ምርጫ አለኝ
ሁሌ እላለሁ
ሁሌ እላለሁ በል በርታ
ገና በቀን ልቤ አትረታ
ሃሳቤም እግር ባይኖረው
ህልሜንም እንከን ቢገጥመው
ምኞቴም እንደ ጉም በናኝ
ስጋየም የከፋው መናኝ
ቢሆንም
እኔ አልተውም ዛሬም
ዳግም ሰማይ መንካት ማለም
እደርሳለሁ
እደርሳለሁ ሩቅ
ያለኝ አቅም ግዙፍ ነው ጥልቅ
ቋጥኝ ለመናድ ስጥር
ያደናቀፈኝ ጠጠር
ያሰብሁት ሩቅ ለመጓዝ
የቀጨኝ የቁጠርሁት ጓዝ
ጓዙ ሸክሙ ያነሰ
ቀድሞ ካለመው ደረሰ
መርከብ ከወደብ ሲያርፍ
መቸ ማዕበሉን ሳያልፍ
ሁሌ እላለሁ
ሁሌ እላለሁ አይዞኝ
ገና ብዙ ምርጫ አለኝ
ሁሌ እላለሁ
ሁሌ እላለሁ በል በርታ
ገና በቀን ልቤ አትረታ
ከተሰፋው መንገድ ያልወጣ
ቢወድቅም መነሻ አያጣ
ደክሞኛልኝ አትበል ስጋየ
ለሞትም አለው ትንሣኤ
ሁሌ እላለሁ
ሁሌ እላለሁ አይዞኝ
ገና ብዙ ምርጫ አለኝ
እደርሳለሁ
እደርሳለሁ ሩቅ
ያለኝ አቅም ግዙፍ ነው ጥልቅ
ሁሌ እላለሁ
ሁሌ እላለሁ አይዞኝ
ገና ብዙ ምርጫ አለኝ
እደርሳለሁ
እደርሳለሁ ሩቅ
ያለኝ አቅም ግዙፍ ነው ጥልቅ
ሁሌ እላለሁ
ሁሌ እላለሁ አይዞኝ
ገና ብዙ ምርጫ አለኝ
እደርሳለሁ
እደርሳለሁ ሩቅ
ያለኝ አቅም ግዙፍ ነው ጥልቅ