Оберіть трек для відтворення
የሠርጋችን ውል ሳይረሳ ወለደች ሳይሉኝ ጋቢ ነክሳ
ቤት ይፈርሳል ወይ በይሉኝታ ችግር ላይፈታ በዝምታ
አታሳየው ቤቴን ገበናዬን ለታሪክ ጎረቤት የጓዳዬን አፈሰህ እንባዬን
ተዉ አታዉጣዉ ስሜን ደጅ ህመሜን
በፍቅር እንፍታው ትዳር ህልሜን አትስበረዉ ቅስሜን
ህመሜን ህመሜን ልፋቴ ድካሜን
ህመሜን ህመሜን ልየው እንዳለሜን
በቀለስነዉ ጎጆ ፍሬ ሳናፈራ
እስከየት ተኮራርፈን እንግባ አንድ ጣርያ
ሳላይህ አትየኝ እኔን እንደ ጠላት
ሳይዘጋ ያድራል ተው የፉክክር ቤት
መግባባት እያለ ወዳጅ ተወቃቅሶ
ምነዉ ብናድሰው የቤቱን ምሠሦ
ፍቅር ነው ትዳር ትዳርም ፍቅር
እኛው እንታረቅ እንነጋገር
ተዉ ስማኝማ ተው ስማኝማ
አታሳየው ቤቴን ገበናዬን ለታሪክ ጎረቤት
የጓዳዬን አፍሰህ እንባዬን
ተዉ አታዉጣዉ ስሜን ደጅ ህመሜን
በፍቅር እንፍታው ትዳር ህልሜን አትስበረዉ ቅስሜን
ህመሜን ህመሜን ልፋቴ ድካሜን
ህመሜን ህመሜን ልየው ውድ ዓለሜን
አይደምቅ የቤቱ እልፍኝ በአንድ ክር ኩራዝ
በአካል ተለያይተን ሳይሞቅ ሳንያያዝ
በልቤ ያኖርኩት ያንተን ፍቅር መንበር
አጥቶ መደገፊያ እንዳይሠባበር
ዘመም ያለን ጎጆ ሀሜት ይጨርሳል
ደጅ ይሁን አይግባ ይቅር ሶስተኛ ሰው
ፍቅር ነው ትዳር ትዳርም ፍቅር
እኛው እንታረቅ እንነጋገር
ተዉ ስማኝማ ስማ በል ስማኝማ ስማ