Оберіть трек для відтворення
ቅን መሳይ አዋላይ ግን
ጥልቅ በሳል መሳይ ግን ጅል
የእጅ አስጥሎ አይኔን አስጨፍኖ
ብርሀን ጥሎ ሳያይ ታይቷል ብሎ
ጤነኛው ቀልቤን ጥዬ
ቢጤዬን ያውቃል ብዬ
እይ ተብዬ ሳላይ ተከትዬ
የእጄን ጣልኩኝ ሰው ጨብጧል ብዬ
በእኛ ዘመንስ ቢባል ቢሉ ድሮን ተሻለ
መልስ የለም ጥፋት እንጂ ጥበብ በፊት መች አለ
አይንን እያላመኑ ታሪክ ታሪክ እያሉ
ባላዩት ያላዩትን ይጋጫል መመሰሉ
ከንቱ ተረክ እንጂ አይተርፍ ከውሸት ውጪ
ጭፍን ሰበብ የውሸት እውቀት ጥበብ
ካለስ አይቶ ማመን አይቶም አለው ማመን
እየካዱ ያስሩታል መንገዱ
ከንቱ ተረክ እንጂ አይተርፍ ከውሸት ውጪ
ጭፍን ሰበብ የውሸት እውቀት ጥበብ
ካለስ አይቶ ማመን አይቶም አለው ማመን
እየካዱ ያስሩታል መንገዱ
ቅን መሳይ አዋላይ ግን
ጥልቅ በሳል መሳይ ግን ጅል
የእጅ አስጥሎ አይኔን አስጨፍኖ
ብርሀን ጥሎ ሳያይ ታይቷል ብሎ
ጤነኛው ቀልቤን ጥዬ
ቢጤዬን ያውቃል ብዬ
እይ ተብዬ ሳላይ ተከትዬ
የእጄን ጣልኩኝ ሰው ጨብጧል ብዬ
ጥንት የነበረው ሞቷል
ያሁንም አልነበረም
ይህ ሰው ዛሬ ተወልዶ
የራሱንም አልኖረም
መስሎት የሌለ ያየው
ከሰማይ የነበረው
ምን ሊውጠው ነው ያኔ
ሲጠየቅ በፈጠረው
ከንቱ ተረክ እንጂ አይተርፍ ከውሸት ውጪ
ጭፍን ሰበብ የውሸት እውቀት ጥበብ
ካለስ አይቶ ማመን አይቶም አለው ማመን
እየካዱ ያስሩታል መንገዱ
ከንቱ ተረክ እንጂ አይተርፍ ከውሸት ውጪ
ጭፍን ሰበብ የውሸት እውቀት ጥበብ
ካለስ አይቶ ማመን አይቶም አለው ማመን
እየካዱ ያስሩታል መንገዱ
ከንቱ ተረክ እንጂ አይተርፍ ከውሸት ውጪ
ጭፍን ሰበብ የውሸት እውቀት ጥበብ
ካለስ አይቶ ማመን አይቶም አለው ማመን
እየካዱ ያስሩታል መንገዱ
ከንቱ ተረክ እንጂ አይተርፍ ከውሸት ውጪ
ጭፍን ሰበብ የውሸት እውቀት ጥበብ