የኔ አመል
ወድጄ መጥላት አልችልበትም አልችልበትም
ቀርቤ መራቅ አላውቅበትም አላዉቅበትም
የኔ አመል አንድ ነዉ አይለወጥም
በወረት ማእበል አይናወጥም
አንቺም ካንደበትሽ የሚወጣዉን
አምኜ እንድቀበል የምሰማዉን
የምትዪኝ ሁሉ እዉነት ለመሆኑ
እርቀን ሳንሄድ ልወቀዉ ካሁኑ
ሰበብ ላታበዢብኝ ምክንያት ላትደረድሪ
ግማሽ አካሌ ሆነሽ ከኔ ጋራ ልትኖሪ
ቃልሽ የማይለወጥ ከሆነነዉ በይኛ
እስኪ በፈጣሪ ስም ምለሽ አረጋጊኝ
ቀርበሽ እንደማትርቂኝ
እንደማትርቂኝ እንደምታዛልቂኝ
ሳምንሽ እንደማትከጂኝ
መቼም እንደማትጎጅኝ
አያን አይኔን እያየሽ ንገሪኛ በይ አዉሪኛ
እኔም ተማምኜ እንድቀርብሽ አድርጊኛ
አያን አይኔን እያየሽ ንገሪኛ በይ አዉሪኛ
ልቤን ተማምኜ እንድሰጥሽ አድርጊኛ
አዝማች
ሰዉም እንደ አየሩ ፀባይ ይቀየራል
ሁሉንም እንደራስ ማመን ይቸግራል
በሰዉ የጠላሁት እንዳያደርስብኝ
ስለዚህ ነዉ ልቤ የሚሰጋብኝ
ሀሳብ ዉጥኔ መክኖ ቅዠት እንዳይሆን ህልሜ
ስሜቴ እንዳይጎዳ እዳይሰብረ ቅስሜ
ዛሬ የምትይዉን ነገም የምትደግሚዉን
አንብቢልኝ ልብሽ ላይ ፅፈሽ ያስቀመጥሺዉን
ቀርበሽ እንደማትርቂኝ
እንደማትርቂኝ እንደምታዛልቂኝ
ሳምንሽ እንደማትከጂኝ
መቼም እንደማትጎጅኝ
አይን አይኔን እያየሽ ንገሪኛ በይ አዉሪኛ
እኔም ተማምኜ እንድቀርብሽ አድርጊኛ
አይን አይኔን እያየሽ በይ አዉሪኛ አናግሪኛ
ልቤን ተማምኜ እንድሰጥሽ አድርጊኛ
ቀርበሽ እንደማትርቂኝ
እንደማትርቂኝ እንደምታዛልቂኝ
ሳምንሽ እንደማትከጂኝ
መቼም እንደማትጎጅኝ
አይን አይኔን እያየሽ ንገሪኛ በይ አዉሪኛ
እኔም ተማምኜ እንድቀርብሽ አድርጊኛ