Оберіть трек для відтворення
እንዳልመጣ ስፍራውም ይርቃል ያለህበት ቦታ
እንዳልቀር መቼ ሰላም ሰጠኝ ያልቋጨሁት ፍቅር
በመሃል መምጣቱም መቅረቱም አልሆንልሽ ብሎኝ
በር እንዳያስተኛኝ አባብሎኝ አባብሎኝ
የሃሳቤን ቁልቁለት የሃሳቤን አቀበት
ስጋግር ዛሬስ የለኝም ጉልበት
ስጋግር ዛሬስ የለኝም ጉልበት
እንዴት ለብቻዬ ያንን ጫካ ልድፈር
እንዴት ለብቻዬ ይህን ሰቀቀን ልስፈር
ሌላሚስጥር የለው ጊዜነው ምትሃቱ
ውዱን ያረከሰ አንተን ያረገ አንቱ
አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ
አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ
ልቤን ጅብ በበላዉ ባወጣው አጥንቱን
ልቤን ጅብ በበላዉ ባወጣው አጥንቱን
የማይችለው ቦታ ማን ግባአለው ጥንቱን (አሃሃሃ)
የማይችለው ቦታ ማን ግባአለው ጥንቱን (አሃሃሃ)
በድሎኝ በድሎኝ በደሉ ልክ የለው
በድሎኝ በድሎኝ በደሉ ልክ የለው
ተመልሼም እዛው ይህ ልቤ ልብ የለው (አሃሃሃ)
ተመልሼም እዛው ይህ ልቤ ልብ የለው (አሃሃሃ)
አዬ አዬ አዬ ...
አዬ አዬ አዬ...
እንዳልመጣ ስፍራውም ይርቃል ያለህበት ቦታ
እንዳልቀር መቼ ሰላም ሰጠኝ ያልቋጨሁት ፍቅር
በመሃል መምጣቱም መቅረቱም አልሆንልሽ ብሎኝ
በር እንዳያስተኛኝ አባብሎኝ አባብሎኝ
የሃሳቤን ቁልቁለት የሃሳቤን አቀበት
ስጋግር ዛሬስ የለኝም ጉልበት
ስጋግር ዛሬስ የለኝም ጉልበት
ባህር ገብቶ ያርፋል ዓባይ ቢንደረደር
የኔ ሃሳብ ጅረቱን ከየት ደርሶ ይደር
አንተ ልብ አዋቂ እኔ ልብ የለኝ
ስትመጣ የምቀበል ስትሄድ የምሸኝ
አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ
አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ
ወይ ፈርቼ አልቀረሁ ወይ ደፍሬ አልመጣሁ
ወይ ፈርቼ አልቀረሁ ወይ ደፍሬ አልመጣሁ
በሌለብኝ አመል በአንተ ልቤን አጣሁ (አሃሃሃ)
በሌለብኝ አመል በአንተ ልቤን አጣሁ (አሃሃሃ)
በእናቴም ብልህ ነኝ ጀግና ነኝ በአባቴ
በእናቴም ብልህ ነኝ ጀግና ነኝ በአባቴ
ልበቢስ ያረገኝ ፍቅሩነው ጠላቴ (አሃሃሃ)
ልበቢስ ያረገኝ ፍቅሩነው ጠላቴ (አሃሃሃ)
አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ
አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ
አዬ እንዳልመጣ ፈራሁ
አዬ እንዳልቀር ጨነቀኝ
አዬ አለሁኝ በመሃል ቤት
አዬ እኔ አንዱም ተስኖኝ
አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ አዬ