Оберіть трек для відтворення
ትዝ ይለኛል ትዝ ትዝ ትዝ
ትዝ ይለኛል ትዝ ትዉስ ትዉስ
አብረን ያሳለፍነው ዘመን
መቼም መቼም መቼም ቢሆን
ለኔም ላንቺም ነው ትዝታ
አይረሳም አንዴ ላፍታ
ትዝ ይለኛል ትዝ ትዝ ትዝ
ትዝ ይለኛል ትዝ ትዉስ ትዉስ
አብረን ያሳለፍነው ዘመን
መቼም መቼም መቼም ቢሆን
ለኔም ላንቺም ነው ትዝታ
አይረሳም አንዴ ላፍታ
እኔ አስብሻለሁ አስቢኝ አደራ
ውዬ አድሬ አላውቅም ስምሽን ሳልጠራ
አልጠገን አለኝ አልቃናልህ
ፍቅሬ ያንቺ አፍቃሪ ሌላ አልወድልህ
ስንቱን ልግለፅልሽ ስንቱን ተናግሬ
መልካምነትሽን ለሰሚ ዘርዝሬ
እቱ አንደበትሽ ጣፋጭ እንደማር
ውበት ቁምነገርሽ ተፈጥሮሽ ፍቅር
ትዝ ይለኛል ትዝ ትዝ ትዝ
ትዝ ይለኛል ትዝ ትዉስ ትዉስ
አብረን ያሳለፍነው ዘመን
መቼም መቼም መቼም ቢሆን
ለኔም ላንቺም ነው ትዝታ
አይረሳም አንዴ ላፍታ
ትዝ ይለኛል ትዝ ትዝ ትዝ
ትዝ ይለኛል ትዝ ትዉስ ትዉስ
አብረን ያሳለፍነው ዘመን
መቼም መቼም መቼም ቢሆን
ለኔም ላንቺም ነው ትዝታ
አይረሳም አንዴ ላፍታ
አዛኝ ይሁንልኝ ያንቺ ልብ ለኔ
እንዲጠገንልኝ የተጎዳው ጎኔ
ስትሄጂ ሸኝቼሽ ትዝታሽ ቀርቶኛል
አንድ ጊዜ እያፅናና አንዴ ያስጨንቀኛል
መቼም ሰው ነኝ እና እጠራጠራለሁ
ስለተራራቅን በብዙ አስባለሁ
አስችሎሽ ጨክነሽ ብትረሽኝ ድንገት
እኔ ረሳሻለሁ ማለት ግን ነው ዘበት
ትዝ ትዝ ይለኛል እንዴት ረሳለሁ
አካሌ ቢርቅህ ሃሳቤ አንተ ጋ ነው
ባይሆንልኝ እንጂ መምጣት ካለህበት
ይናፍቃል ውስጤ ትዝታህ አለበት
ካንተ ተለይቼ አስችሎኝ ብኖርም
ሃሳቤ ተሳክቶ መመለሴ አይቀርም
በደስታ እስኪያነባ ዐይኔ ዐይንህን አይቶ
ፍቅርህ ያሞቀኛል በልቤ ውስጥ ገብቶ
ስንቱን ልግለፅልሽ ስንቱን ተናግሬ
መልካምነትሽን ለሰሚ ዘርዝሬ
እቱ አንደበትሽ ጣፋጭ እንደማር
ውበት ቁምነገርሽ ተፈጥሮሽ ፍቅር
መቼም ሰው ነኝ እና እጠራጠራለሁ
ስለተራራቅን በብዙ አስባለሁ
አስችሎሽ ጨክነሽ ብትረሽኝ ድንገት
እኔ ረሳሻለሁ ማለት ግን ነው ዘበት