Оберіть трек для відтворення
ለኔ አዲስ ነሽ ዉዴ
ነሽ ዉዴ ነሽ ውዴ
ሁሌም ነሽ ለኔ አዲስ
ሁሌ አዲስ ነሽ ውዴ
በእጄ እስክትገቢልኝ እስከሚያቅፍሽ ክንዴ
አይደለም መውደዴ
ቢሳሳ ነው እንጂ ያልጠገበሽ ሆዴ
አይጠግብሽም ሆዴ
የብርቅ የኔ ቅመም ደማማ መውደዴ
እናና ዘመዴ
የብርቅ የህይወት ቅመም ደማም ነሽ መውደዴ
እናና ዘመዴ
አንቺኑ ነው ያልኩት ወድጄሽ ከሆዴ
ወድጄሽ ከሆዴ
መች ዓይኔስ ሆነና ከላይ አይቶሽ ብቻ
ከላይ አይቶሽ ብቻ
መች ድሮስ ሆነና ካንገት በላይ ምርጫ
ካንገት በላይ ምርጫ
ልቤ አንቺን እንጂ መች መልክሽን ብቻ
መች አየ እሱን ብቻ
መች ይተውሽ ነበር ዓይኔስ ቢያሽ ድሮ
ባይኖር እንኳን መልክሽ ውብ ባትሆኚም ኖሮ
ቢደምቅም ባይደምቅም ቢበርደው ቢሞቀው
ላይሽ ብቻ አይደለም ድንቄን የደመቀው
ከላይ እይኝ ባለች ባደባባይቷ
አንቺ አትመዘኚም በብልጭልጪቷ
ጥቁርም ነጭም ቢሆን የጠጉርሽ ቀለሙ
መች እሱ ሆነና ለኔ ብርቅ ዓለሙ
አይጭንቅሽ አንቺ ሆኖ አይሰለቸኝም
ጉዳዬ ውስጥሽ ነው ካንቺ አይበልጥብኝም
መልክሽ አይበልጥሽም እንዳለሽም ባውቀው
አንቺው ነሽ መብራቷ ፍቅር የምታደምቂው
ዉብ ቢሆንም በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ዉብ ቢሆንም በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ለኔ አዲስ ነሽ ዉዴ
ነሽ ዉዴ ነሽ ውዴ
ሁሌም ነሽ ለኔ አዲስ
ሁሌ አዲስ ነሽ ውዴ
በእጄ እስክትገቢልኝ እስከሚያቅፍሽ ክንዴ
አይደለም መውደዴ
ቢሳሳ ነው እንጂ ያልጠገበሽ ሆዴ
አይጠግብሽም ሆዴ
የብርቅ የኔ ቅመም ደማማ መውደዴ
እናና ዘመዴ
የብርቅ የህይወት ቅመም ደማም ነሽ መውደዴ
እናና ዘመዴ
አንቺኑ ነው ያልኩት ወድጄሽ ከሆዴ
ወድጄሽ ከሆዴ
መች ዓይኔስ ሆነና ከላይ አይቶሽ ብቻ
ከላይ አይቶሽ ብቻ
መች ድሮስ ሆነና ካንገት በላይ ምርጫ
ካንገት በላይ ምርጫ
ልቤ አንቺን እንጂ መች መልክሽን ብቻ
መች አየ እሱን ብቻ
ጊዜ ሲለዋወጥ ወራቱ ሲጨምር
ይነጥፍ የለም ወይ ውበት ቢሆን ጠጉር
እንኳን ሲበስልና አድሮ ቀን ሲከብደው
መልክማ ይቀየራል ላንዳፍታም ቢበርደው
ላዩማ አላፊ ነው መልክና ደምግባት
ሁሌም ግን አያልፍም ብርቄ የልብሽ ውበት
ጊዜ ሲለዋወጥ ወራቱ ሲጨምር
ይነጥፍ የለም ወይ ውበት ቢሆን ጠጉር
እንኳን ሲበስልና አድሮ ቀን ሲከብደው
መልክማ ይቀየራል ላንዳፍታም ቢበርደው
ላዩማ አላፊ ነው መልክና ደምግባት
ሁሌም ግን አያልፍም ብርቄ የልብሽ ውበት
ዉብ ቢሆንም በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ዉብ ቢሆንም በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ዉብ ቢሆንም በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም
ዉብ ቢሆንም በርግጥም
መልክሽ ካንቺ አይበልጥም
ምን ቢሆን ከውጪም
አንቺ አትለወጪም