Оберіть трек для відтворення
የሚነጣው ሁሉ የሚጠቁረውም ሰው
የቀይ ዳማውም ሰው
በክፉ አይነሳም ከሷ ፊት ማንም ሰው
ከሷ ፊት ማንም ሰው
የሚነጣው ሁሉ የሚከላለሰው
በክፉ አይታማም ከሷ ፊት ማንም ሰው
ከሷ ፊት ማንም ሰው
ቢያሞቁ ቢያካብቧት
ቢያደምቁ ወይ ቢክቧት
አታልፍም ግቡ ግን ሰምታ
ያስከፍታል ሀሜታ
ያስከፍታል ሀሜታ
ያስከፍታል ሀሜታ
በእናት ወይ ባባቷ በዘር ተዋልዷታል
ዘመድ ናት እቺ ልጅ ይመለከታታል
አለች ቆጣ ቆጣ ፊትዋን ከፋው እሷ
የሩቅ አርገው ቢያሙት ጠይም ሰው ለራሷ
ጥቁርስ ቢታማ እንዴት አያማትም
ጠይም ናት ልጅቷ ባዕድ ሰው የላትም
አፉን አስያዘችው ያንተው ይባስ ብላ
ከኔ አይቀርቡሽ ባዩን ሀሜተኛን ሁላ
ቆጣ አረጋትና ወገን እንደሌላት
ልኩን አሳየችው እሷስ የማን ዘር ናት
የሚነጣው ሁሉ የሚጠቁረውም ሰው
የቀይ ዳማውም ሰው
በክፉ አይታማም ከሷ ፊት ማንም ሰው
ከሷ ፊት ማንም ሰው
የሚነጣው ሁሉ የሚከላለሰው
በክፉ አይታማም ከሷ ፊት ማንም ሰው
ከሷ ፊት ማንም ሰው
የደም ውልድ ናት ወዳጅ
ከውስጥ ሆነ ከደጅ
ፍቅር ነው መለኪያዋ
ሁሉም ዘመድ ስጋዋ
ሁሉም ዘመድ ስጋዋ
ሁሉም ዘመድ ስጋዋ
በእናት ወይ ባባቷ በዘር ተዋልዷታል
ዘመድ ናት እቺ ልጅ ይመለከታታል
አለች ቆጣ ቆጣ ፊትዋን ከፋው እሷ
የሩቅ አርገው ቢያሙት ጠይም ለራሷ
ጥቁርስ ቢታማ እንዴት አያማትም
ጠይም ናት ልጅቷ ባዕድ ሰው የላትም
አፉን አስያዘችው ያንተው ይባስ ብላ
ከኔ አይቀርቡሽ ባዩን ሀሜተኛን ሁላ
ቆጣ አረጋትና ወገን እንደሌላት
ልኩን አሳየችው እሷስ የማን ዘር ናት
እያለች የራሴ ስጋዬና ነፍሴ
አትሙብኝ አለች ሰው ያሙባት ጊዜ
ከዚያ ጫፍ እስከ ጫፍ የቱም ሰው ሲነሳ
የሷ ሰው ነው ለካ ቆረቆራት እሷ