Оберіть трек для відтворення
በእንዳሻን አንጓዝ በቃ
ቀርቷል የብቻ ፈቃድ
አልፏል ነጠላነቴ
ተጣምሯል ከሷ ህይወቴ
ነይ ግቢ እያልኳት
እንዲሞቅ ባዶ ቤቴ
ተጣምሯል ህይወቷ ከህይወቴ
ውልብ እንኳን ቢለኝ ላጤው ህይወት
የብቻነቱ ነፃነት
አምኖ ልቤ
ወድጃት ፈቅዷት ቀልቤ
ልጋራ ሂዎትን ከሷ ጋራ
ባሻኝ ልደር የለ ላንዷ ነፍሴ
አብቅቷል የላጤው ጊዜ
በእንዳሻን አንጓዝ በቃ
ቀርቷል የብቻ ፈቃድ
አልፏል ነጠላነቴ
ተጣምሯል ከሷ ህይወቴ
ነይ ግቢ እያልኳት
እንዲሞቅ ባዶ ቤቴ
ተጣምሯል ህይወቷ ከህይወቴ
ውልብ እንኳን ቢለኝ ላጤው ህይወት
የብቻነቱ ነፃነት
አምኖ ልቤ
ወድጃት ፈቅዷት ቀልቤ
ልጋራ ሂዎትን ከሷ ጋራ
ወዶ መዋደድን የተጠማ ሰው
ሊከፍል ይገደዳል ፍቅር እንዲያርሰው
የፍሬውን ምላሽ ቢፈልግ ነው እንጂ
ሰሪ ለምን ፈቅዶ ዘር ይጥላል በእጅ
እኔ እሷን ስወዳት የወደደች እኔን
ፈቅደን አንግሰን ነው ፍቅርን ተማምለን
በብቻዬ ፍቃድ እንደሮጥኩት ያኔ
ዛሬ ተቀንሷል ወደሷ መብት የኔ
በእንዳሻን አንጓዝ በቃ
ቀርቷል የብቻ ፈቃድ
አልፏል ነጠላነቴ
ተጣምሯል ከሷ ህይወቴ
ነይ ግቢ እያልኳት
እንዲሞቅ ባዶ ቤቴ
ተጣምሯል ህይወቷ ከህይወቴ
ውልብ እንኳን ቢለኝ ላጤው ህይወት
የብቻነቱ ነፃነት
አምኖ ልቤ
ወድጃት ፈቅዷት ቀልቤ
ልጋራ ሂዎትን ከሷ ጋራ
ለራስ ብቻ ቢባል ኪዳን አይሳካም
ፍቅርን ከመጎምጀት ሰው ከጥም አይረካም
ወደው ካልኖሩለት ለፍቅር በፍቅር
ያልዘራው አይበቅልም ሰው ምንም ቢቆፍር
ክብርን ሳያሳዩት ኪዳንን ተግብረው
ፍቅር አይገኝም ቢሽቱም አምርረው
ነፃ መብቴን ብዬ ፍቅሯን ከማቅማማ
ላካፍላት ከመብቴ እሷን ከምጠማ
ነይ ግቢ እያልኳት
እንዲሞቅ ባዶ ቤቴ
ተጣምሯል ህይወቷ ከህይወቴ
ውልብ እንኳን ቢለኝ ላጤው ህይወት
የብቻነቱ ነፃነት
አምኖ ልቤ
ወድጃት ፈቅዷት ቀልቤ
ልጋራ ሂዎትን ከሷ ጋራ
ነይ ግቢ እያልኳት
እንዲሞቅ ባዶ ቤቴ
ተጣምሯል ሂዎቷ ከህይወቴ
አምኖ ልቤ
ወድጃት ፈቅዷት ቀልቤ
ልጋራ ህይወትን ከሷ ጋራ