Оберіть трек для відтворення
ጎዳናው ጎዳናው ጎዳናው ጎዳናው መንገድ
አንድም የሚጠላ ያመጣል አንድ የሚወደድ
ጎዳናው ጎዳናው ጎዳናው ጎዳናው መንገድ
አንድም የሚጠላ ያመጣል አንድ የሚወደድ
አንድም የሚጠላ ያመጣል አንድም የሚወደድ
ገረመኝ ገረመኝ ኧረ እኔን ገረመኝ ገረመኝ
አመመኝ አመመኝ
ምነው ባልሰማሁ አልኩ ባልነገሩኝ
ወይ ካንቺ ጋር ፍቅር ባልጀመርኩኝ
ምነው ባልሰማሁ አልኩ ባልነገሩኝ
ወይ ካንቺ ጋር ፍቅር ባልጀመርኩኝ
ሳላይሽ እንዳትሄጂ ማነው የመከረሽ እናትዬ
ደግ ወዳጅሽ ነው ወይ መጥፊያሽን ያሳየሽ የኔ ቆንጆ
አላነድም እሳት አላሞቅም ቤቱን እናትዬ
ባንቺም አልወደድኩት ማንደዱም ማጥፋቱን የኔ ቆንጆ
ያራተኛው ጣትሽ ቀለበት
አይወድቅም ነበረ በጉልበት
ወደቀብሽ አሉ በቀላሉ
ለካስ ገላ ያከሳል ቃል ማጉደሉ
ያራተኛው ጣትሽ ቀለበት
አይወድቅም ነበረ በጉልበት
ወደቀብሽ አሉ በቀላሉ
ለካስ ገላ ያከሳል ቃል ማጉደሉ
ጎዳናው ጎዳናው ጎዳናው ጎዳናው መንገድ
አንድም የሚጠላ ያመጣል አንድ የሚወደድ
ጎዳናው ጎዳናው ጎዳናው ጎዳናው መንገድ
አንድም የሚጠላ ያመጣል አንድ የሚወደድ
አንድም የሚጠላ ያመጣል አንድ የሚወደድ
ገረመኝ ገረመኝ ኧረ እኔን ገረመኝ ገረመኝ
አመመኝ አመመኝ
ምነው ባልሰማሁ አልኩ ባልነገሩኝ
ወይ ካንቺ ጋር ፍቅር ባልጀመርኩኝ
ምነው ባልሰማሁ አልኩ ባልነገሩኝ
ወይ ካንቺ ጋር ፍቅር ባልጀመርኩኝ
አሁን ምን ያደርጋል እድሜሽን ብቆጥረው እናትዬ
አንሼሽ ማደሬን መበለጤን ሳውቀው የኔ ቆንጆ
አምላክ ስለሰራት ምድርን በክብነት እናትዬ
ዞሮ አይመጣ የለም ወደነበረበት የኔ ቆንጆ
የወዳጅን ነገር ሳስበው
መምጣትዋም መሄድዋም ህልም ነው
ይቺን እንቆቅልሽ ፈቺው ማነው
ትናንት የኔ ገላ ዛሬ የሰው ሰው
የወዳጅን ነገር ሳስበው
መምጣትዋም መሄድዋም ህልም ነው
ይቺን እንቆቅልሽ ፈቺው ማነው
ትናንት የኔ ገላ ዛሬ የሰው ሰው
ምን ወጣኝ ምን ወጣኝ ምን ወጣኝ
ምን ወጣኝ ምን ወጣኝ ምን ወጣኝ
አለሁ እንጂ ፍቅርሽ እንደቀጣኝ 
ምን ወጣኝ ምን ወጣኝ