Оберіть трек для відтворення
ይህንን ፍቅር የሚጥም ስጦታ
በከንቱ አትየው አታመንታ ላፍታ
ንፁህ ነው ልቤ ብታምንም ባታምንም
ሳትፈልግ ብትቀር እኔ የለሁበትም
የለሁበትም እኔ የለሁበትም
ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም
የለሁበትም እኔ የለሁበትም
ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም
ለምን ልጠራጠር ለምንስ ልስጋ
ባንተ ላይ በገዛ ፍቅሬ
በዝምታ ድምበር ኧረ እንዴት ልኑር
ባንተ ታጥሬ
የሚዘገይ ተስፋ ማሳዘኑ አይቀር ልቦና
እጅግ ሰባብሮ
እኔ የለሁበትም ቢገባህ መልካም
ፍቅሬ ውሎ አድሮ
የለሁበትም እኔ የለሁበትም
ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም
የለሁበትም እኔ የለሁበትም
ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም
እንዴት ሳልጠይቅህ
ብዬ እንዳይቆጨኝ መስውአት ሆኛለሁና
ጥፋትክን አይቼ መኖር አልችልም
ብዙ ነው እና
ልብህ ሰነፍ አይሁን
ምንጊዜም ምክር ወዳጄ ተግሳፅ አትጥላ
ኋላ አስጨክነኸኝ
የለሁበትም ብሆን የሌላ
የለሁበትም እኔ የለሁበትም
ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም
የለሁበትም እኔ የለሁበትም
ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም
ይህንን ፍቅር የሚጥም ስጦታ
በከንቱ አትየው አታመንታ ላፍታ
ንፁህ ነው ልቤ ብታምንም ባታምንም
ሳትፈልግ ብትቀር እኔ የለሁበትም
የለሁበትም እኔ የለሁበትም
ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም
የለሁበትም እኔ የለሁበትም
ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም
የጋራ ነው ሲባል
ሁሉም አምኖበት ተዋዶ አብሮ እየኖረ
ምነው በኔ ብቻ
ወድቆብኝ ፍቅር ሚዛኑ ዞረ
ትጋቴ ነው ሀብቴ
አንተን ለማረም ጊዜዬን ሰጥቼሀለሁ
ላይ ላዩን እየኖርን
ካልተረዳኸኝ ምን አደርጋለሁ
የለሁበትም እኔ የለሁበትም
ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም
የለሁበትም እኔ የለሁበትም
ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም
የለሁበትም እኔ የለሁበትም
ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም
የለሁበትም እኔ የለሁበትም
ውርድ ከራሴ እኔ የለሁበትም