Оберіть трек для відтворення
ወይ ብሬ ወይ ብሬ ወይ ብሬ ወይ ብሬ
አንገራግራለው ድንጉጥ ኩሩ መሳይ
ቀኑ እየመሸብኝ አንቺን ሳይ አንቺን ሳይ
ሞላሽ ጎደልሽ ስል ልክሽ እያሳሳኝ
ቀን እየመጣብኝ አንቺን ሳይ አንቺን ሳይ
መከታ ናት ብለው አትመናት አለኝ
ክብር ልንሳት ብለው ገንዘብህ ናት አለኝ
ጉልበቴ ናት ስለው አታምልካት አለኝ
ማን ልበላት ስለው መዝገብ በላት አለኝ
ታድያ ምን ሆኜ ነው ላርዳርሺኝ ትዳሬ
ከሌለሽ ይፈርሳል ብዬ መጠርጠሬ
መዝገቤ ነሽ እንጂ አይደለሽም ፍቅሬ
ግን አስብሻለው ግዴን ዞሬ ዞሬ
ወይ ብሬ
ከኔም ባትበልጪባት ፊትም ባትሰጥሽ
ከሌለሽ አትወድም ሚስቴም ብትንቅሽ
ሄደህ አትቆይ እንጂ አምጣት ትለኝና
ስቆይ ግን ትላለች ተዋት ምን ጠፋና
መኖርሽ ለኛ እንጂ ላንቺ እኛ አንኖርም
አታስመስይብን ባንቺ የተፈጠርን
ከሚስቴ አትበልጪብኝ ከልቤ አካል ፍቅሬ
ሰርክ አንቺን ግን ሳስብ ምን ሆኜ ነው ብሬ