ሆድዬ
ሆድዬ ምነዉ በአጀቡ ምነዉ በአጀቡ መታጀቡ
ሆድዬ ምነዉ ምን ከፋሽ ምነዉ ምን ከፋሽ
በዚያው ጠፋሽ
ጭንቅ ይላል እንደዋዛ ክብድ ይላል እንደዋዛ
ጥፍት ይላል የሀሳብ ለዘ ወዳጅ ሲሆን
ማልዶ ጤዘ
ቃል አልነበር ወይ እዉነቱ ልብ አልነበር ወይ ፅናቱ
ፍቅርስ አይደል ወይ እምነቱ ሰዉ መሰረቱ
እንዲያዉ መዉደድን አልምዶ
እንዲያዉ ዉስጥ ዉስጡን ስር ሰዶ
መቅረቱስ ማዶ በኔዉ ላያ ፈረዶ
ትርፍ የለዉ ሲሳይ
ጽድቅ የለዉ ለላይ
ትርፍ የለዉ ሲሳይ
ስቃይ ነዉ
ቃል ቃል ቃል ቃል
ቃል አለን ብዬ ቃል አለን ብዬ የኖርኩት ችዬ
ግና ያዉ ነዉ ልብሽ ባየዉ ባየዉ ባየዉ
ልብሽ ያዉ ነዉ ባየዉ ባየዉ
እቴ ገላ አፈር ነዉ (3)
ማፍቀር ካልመዘነዉ
አዝማች
ልቤን ለማዳን ከፀፀት ባልልም ፍቅርን ልመፅወት
ልወቀዉ ካንቺዉ በደሌን ወይ ቃል ማጉደሌን
ሀቅም ባይዳኛት እዉነታ ባልኳት እያልኩኝ ይቅርታ
መሆን አይረታም ተይ ዉሀ ሽታ
ትርፍ የለዉ ሲሳይ
ጽድቅ የለዉ ለላይ
ትርፍ የለዉ ሲሳይ
ስቃይ ነዉ
ቃል ቃል ቃል ቃል
ቃል አለን ብዬ ቃል አለን ብዬ የኖርኩት ችዬ
ግና ያዉ ነዉ ልብሽ ባየዉ ባየዉ ባየዉ
ልብሽ ያዉ ነዉ ባየዉ ባየዉ
እቴ ገላ አፈር ነዉ (3)
ማፍቀር ካልመዘነዉ