ኸረ ሆይ ፥ ኸረ ሆይ
ኸረ በየት ወጣህ አንት የኔ ፀሐይ
አለህ ወይ ፥ አለህ ወይ
ምነው ቅርቤ ሳለህ ሆንክብኝ ሰማይ
ለጨዋታማ ፣ ለጨዋታማ ቤቴ
ለጨዋታማ ስንት ወዳጅ መጥቷል ስንቴ
የለህ እንደሆን አትመጣ እንደሆን...
ባዶ ይሆንብኛል ቤቴ
የኔ ውብ ዜማ ፣ የኔ ውብ ዜማ ፣ ቅኔ
የኔ ውብ ዜማ ዕልፍ ነህና ለኔ
የለህ እንደሆን አትመጣ እንደሆን
መች እንቅልፍ ያውቃል ዐይኔ
ቆላው ውርጭ ይሆናል
ደጋው ይወብቃል
ያላየሁህ እንደው ምን እንዴት ይጥማል
ከዋክብት ጨረቃን ውበት የኳልኳቸው
ስትኖር አይደለም ወይ እኔም የማያቸው
ከማዶ ማዶ - ከማዶ ነው ከልቤ ስር ማዶ
ከማዶ ማዶ - እስክትመጣ ከዋጠው በረዶ
ኸረ ሆይ ፥ ኸረ ሆይ
ኸረ በየት ወጣህ አንት የኔ ፀሐይ?
አለህ ወይ ፥ አለህ ወይ?
ምነው ቅርቤ ሳለህ ሆንክብኝ ሰማይ?
ለጨዋታማ ፣ ለጨዋታማ ቤቴ
ለጨዋታማ ስንት ወዳጅ መጥቷል ስንቴ
የለህ እንደሆን አትመጣ እንደሆን...
ባዶ ይሆንብኛል ቤቴ
እስቲ ና ወዳጄ - የልቤ ዝማሬ
እኔ እንድበረታ - ደክሜያለሁ ዛሬ
አንተው ባይኖቼ ላይ - ስታድር ስትውል
ቆየሁ ካጌጥኩበት - የእናቴን ስርኩል
ከማዶ ማዶ - ከማዶ ነው ከልቤ ስር ማዶ
ከማዶ ማዶ - እስክትመጣ ከዋጠው በረዶ